Duration 22:4

[ፓትርያርኩ መልእክት ልከዋልቲባዋ] ለጳጳሳቱ አሳፋሪ ነገር ተናገረች ፓስተሩ አሁንም አልተፈታም የአስማተኞች ቀን

48 854 watched
0
1.3 K
Published 15 Jan 2022

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳዛኝ ልብ የሚነካ መልእክት ልከዋል መልእክታቸው ምንድ ነው ከንቲባዋ ለጳጳሳቱ ትናንት አሳፋሪ ነገር እንደተናገረች ተገልጻል ከ ስብሰባው ጋ ተያይዞ.. ፓስተሩ ዛሬም አልተፈታም ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ በጦማሩ ላይ ያሰፈረውን የአስማተኞች ቀን የሚለውን ጽሑፍም እንመለከታለን አብራችሁን ቆዩ ለኅሊናው ታማኝ ሆኖ የተገኘውን ፓስተር ፍቱት። መስቀል አደባባይ የማንም ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መሆኑን በግልጽ የተናገረው ፓስተር ቢኒያም ለእሥር እንደተዳረገ እየተነገረ ነው። ፓስተሩ ጥር ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም. «መስቀል አደባባይን እንውረስ» በሚል መርሕ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ይሁንታ በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት አምልኮ ሥርዐት ከብዙኃኑ በመለየት በእውነት እና በሞራል ሚዛን የተሳሳተ እና ቤተ ክርስቲያኗን ሆን ብሎ እንደመተናኮል የሚቆጠር መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱን ፊት ለፊት ወጥቶ በግልጽ አውግዟል። ይህ የፓስተሩ ሐቅን የመግለጥ ተግባር የኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶን እውነት የሚያስረግጥ በመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባለሥልጣናት ዐይን በበጎ የታየ አይመስልም። በመሆኑም የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ፓስተር ቢንያም ጥር ፭ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም. ልጆቹን ትምህርት ቤት አድርሶ ሲመለስ በፖሊስ ታሥሯል። ይህ የፖሊስ ተግባር ሊወገዝ የሚገባው፣ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚጥስ እና ስለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እውነት የሚናገርን ሁሉ ለማፈን የሚደረገው ጥረት አካል እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህም ለኅሊናው ታማኝ የሆነውን ፓስተር ፍቱት ብለን ድምጻችንን ልናሰማ ይገባል። መንግሥት ጆሮ ብቻ ሳይሆን ልብም ሊኖረው ይገባል መንግሥት የሚሰማበት ጆሮ ብቻ ሳይሆን ለብያኔ የተከፈተ ልብም ሊኖረው ይገባል እኩልነት በትክክል እኩልነት የሚሆነው አቅጣጫውን ሳይስት ሲሰራበት ብቻ እንጂ በምንም አይነት ሁኔታ እኩል ሊሆኑ የማይችሉ ሁለት ነገሮችን እኩል ናችሁ በማለት አይደለም ፀሐይ ከጨረቃ ቢልቅ እንጂ ጨረቃ ከፀሐይ እኩል ልሁን ቢል እንደማይቻለው ሁሉ ክርስትና እና ኢስላምም በሄትኛውም ሚዛን ቢመዘኑ እኩል የሚሆኑበት መንገድ የለም ስለዚህ መንግሥት እኩልነት መቻቻል በሚል ቀልዳቀልድ ወሬ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና ይዞታዋ ላይ የሚያደርገውን ቅጥ ያጣ ዝርፍያ እና ቅሚያ ግፍ እና በደል በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል መስቀል ዓደባባይ ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በደሟ ጠብቃ ያቆየችው የደም ዋጋዋ (አንጡራ ሀብቷ)እንጂ የኢስላም ወይም የፕሮቴስታንት ሀብት አይደለም ኢስላም ወገኖቻችንም ብትሆኑ ከእኛ ልምድ ልትወስዱ ይገባል እንጂ ይዞተዎቻችን ቀምታችሁ ልትወስዱ አይገባም ሰው የቤት ባለቤት መሆን ያለበት ሰርቶ እንጂ ቀምቶ እና ዘርፎ አይደለምና ስለዚህ በፍቅር ካየነው ለሁላችንም ይበቃል በሚል የማደንዘዣ እና የሽንገላ ቃላት የቤተክርስቲያንን ይዞታ ጨርሶ ለመንጠቅ የሚደረገው ስውር ዘመቻ ሁሉ ባለበት ሊገታና ሊመክን ይገባል ሁሉም በርስቱ ሁሉም በቤቱ ሊኖር ይገባል ደግሞም ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ አይኖርም የሚለውን ብሂልም መርህ ማድረግ ተገቢ ነው ከሆነም ሰው እንደ ጎረቤቱ መኖር ካስፈለገው ሰርቶ እንጂ ቀምቶና ዘርፎ መሆን የለበትም የቤተክርስቲያን አባቶችም ለግዜው ከሚቀርብላችሁ ግብዣ እና ሽልማት ይልቅ የእባብን መንገድ የምትለዩበት የጥበብ ዐይን ሊኖራችሁ ይገባል እባብ የቱንም ያህል የምስጋና ጎርፍ ቢያጎርፍ እባብ የቱንም ያህል ብሉይ ሐዲስ ጠቅሶ ስለ መላእክት ክብር (ጠባቂነት)ቢመሰክር ማቴ 4:6 እባብ የቱንም ያህል ጩኾ ስለክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ቢመሰክር ሊያስት እንጂ ለሌላ አላማ አይደለምና እንግዲህ ዐዋቂዎች (ልባሞች ሁኑ ትጉም ጠላታችሁ ጋኔን የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና እርሱንም በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት! ፓትርያርኩ ወደላኩት መልእክት ስናልፍ “ከሕማሜ ይልቅ የመስቀል ዐደባባይ ነገር ይበልጥ ያሳስበኛል” ብለዋል! ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በእርሳቸው ሆስፒታል መግባት ከከንቲባዋ ይደረጋል የተባለው ስብሰባ ላልተወሠነ ጊዜ መተላለፉን ሲሰሙ የተናገሩት ቃል ነው። ፩. በእርሳቸው አለመገኘት ምክንያት ቀኑ ተላልፎ ተረሳስቶ እንዳይቀር ለዚህ ስብሰባ ብቻ ቀኖናው በሚፈቅደው መሠረት ከአረጋዊያኑ ወይም በፓትርያርኩ ውክልና የሲኖዶሱ ጸሐፊ እንዲመሩት ቢደረግ፣ ፪. ከንቲባዋ እኔ ቢሮ ወይም ሸራተን እንሰብሰብ ማለታቸው የተሰማ ሲኾን አቡነ ዮሴፍ ግን ወደ መንበረ ፓትርያርክ እርሳቸው መምጣት እንዳለባቸው በጽኑ አሳስበዋል። አበው በዚህ አቋም ቢጸኑ፣ ፫. ከከንቲባዋ ጋር የሚደረገው ውይይት ከመስቀል ዐደባባይ ከፍ ያለ ቢኾን። ፬. አሰላለፋቸውን ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተ መንግሥቱ ለማድረግ የሚራወጡ ሰዎች ዐርፈው እንዲቀመጡ የመጨረሻ ተግሣጽ ቢሰጣቸው። የቅዱስነታቸው ጤንነት ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መኾኑም ታውቋል።

Category

Show more

Comments - 155